ምሳሌ 1 ፡ 7፡ እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ ተላሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
7 እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው ፤ ተላሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
29 ዕውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርንም መፍራት ስላልመረጡ፣ 30 ምክሬን ለመቀበል ስላልፈለጉ፣ ዘለፋዬን ስለ ናቁ፣ 31 የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ። 32 ብስለት የሌላቸውን ስድነታቸው ይገድላቸዋል ፤ ተላሎችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፤ 33 የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል ፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።